1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦፌኮ አመራሮች እስራት፤ የፓርቲው መግለጫ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 19 2016

መንግስት አመራሮቼ እና አባላቶቼ ላይ የሚያደርሰው እስራት እና ደብዛ ማጥፋት ማጥፋት አማሮኛል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመለከተ። ፓርቲው ትናንት ዓርብ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እየደረሰብኝ ነው ያለው የአመራሮች እና አባላት እስራት እና ደብዛ ማጥፋት የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አቋዋሜን አያናውጥምም ብሏል ።

https://p.dw.com/p/4fG6J
Deutschland Äthiopiens Oromo federalist congress |  Merera Gudina
ምስል Eshete Bekele Tekele/DW

የአባላቱ መታሰር እና በመንግስት ላይ የኦፌኮ ምሬት

የኦፌኮ አመራሮች እስራት፤ የፓርቲው መግለጫ

መንግስት አመራሮቼ እና አባላቶቼ ላይ የሚያደርሰው እስራት እና ደብዛ ማጥፋት ማጥፋት አማሮኛል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመለከተ።

ፓርቲው  ትናንት ዓርብ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እየደረሰብኝ ነው ያለው የአመራሮች እና አባላት እስራት እና ደብዛ ማጥፋት የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አቋዋሜን አያናውጥምም ብሏል ።

 በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር የኦፌኮ-ኦነግ ጥምረት

በአገሪቱ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የማይቀያየር አቋም ይዞ በተለያዩ ብርቱ ፈተናዎች ውስጥ ማለፉን በመግለጫው ያስታወቀው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በአገሪቱ በተለያዩ ስርዓቶች ስር የአመራሮች እስራት እና ግድያን ጨምሮ በርካታ ፈተናዎችን ማሳለፉን አብራርቷል።በዚህ ሂደትም ከህግ ውጪ ስወራና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ አላስፈላጊ ያላቸው እርምጃዎች በፓርቲው አመራሮች እና አባላት ላይ መፈጸሙን፥ አማሮ አንስቷል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በመግለጫው ዙሪያ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ከሰሞኑም ስምንት አመራሮቻችን በኦሮሚያ ክልል በሃይል ተሰውረዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት የሰላም ጥሪ፣ ተስፋና ስጋቱ

“ሸመኒ ቤኛ የተባሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተባባሪ ሚያዚያ 9 በአዳማ ከተማ ታስረዋል። ከዚያ አስቀድሞ ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ/ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በቾ ወረዳ የታሰሩት አስተባባሪያቸን ግርማ ጫላ ከሶስት ቀናት በፊት ነው የተለቀቁት። መጋቢት ወር ውስጥ በቱሉ ቦሎ ከተማ የታሰሩ ሶርሳ ሲማ የተባሉ አባላችን እስካሁን ለፍርድ ቤት አልቀረቡም። በተመሳሳይ ወር በሰሜን ሸዋ ፊቼ ከተማ እእነዲሰወሩ የተደረጉት አመራራችን ደጀኔ ግርማ፥ በቡራዩ የታሰሩት የአካል ጉዳተኞች ሊግ አስተባባሪ ከበደ ዋቅጅራ፥ በድሬ ዳዋ ከህግ ውጪ እስር ላይ የሚገኙ አባላችን መሃመድ ዶዮ፥ ከጥቅምት ጀምሮ ዱካቸው የጠፋው የምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ትቤ ወረዳ አስተባባሪ መለሰ ጫላ እንዲሁም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተባባሪ ፍቃዱ አያና እስርና ስወራ ተጠቃሸዕ ናቸው” ብለዋል።

የአቶ በቀለ ገርባ ከፓርቲ ፖለቲካ መገለልና አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸው

እነዚህ ሁሉ አመራርና አባላቶቹ የታሰሩት ከህግ ሂደት ውጪ ነው ያለው ኦፌኮ ይፈጠማሉ ያሏቸው ግድያ፥ እስራት እና ስወራዎች እንዳሳሰቡትም አስረድቷል።“ትልቁ ችግር እኮ ፍርድ ቤት ቀርበው ሲፈረድባቸው አናይም” ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ተሰናብተው እስካሁንም በእስር ላይ የሚገኙትን የኦነግ አመራሮችንም በአብነት አንስተዋል። መሰል ድርጊት ድርጅታቸውን በእጅጉ መጉዳቱንም አንስተው ከአራት ዓመት በፊት ከ200 በላይ የነበረው የፓርቲያቸው ማዕከላት አሁን ላይ ወደ ሶስት ብቻ መወሰኑን በማሳያነት አቅርበዋል።

 ለኢትዮጵያው የፖለቲካ ቀውስ የውይይት ጥሪ

የሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ መጥበብ ለመንግስትም ይሁን ለተቃዋሚ አይበጅም ያሉት ፕሮፈሰር መረራ አገሪቱም አላስፈላጊ ያሉት የፖለቲካ ድባብ ውስጥ መግባቷን በትዝብታቸው አንስተዋል። “ሰላማዊ የፖለቲካ አውድ በመዝጋት ከታጣቂ ጋር ታንዛንያ ሄዶ መወያየት የሚያመጣው ውጤት አይኖርም። ያ ታጣቂም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅት ላይ ከሚደርሰው ነገር ምን ተመልክቶ ትጥቅ ወደ መፍታት ይሄዳል? አሁን የኦነግ ሰራዊት አባላት ለምን በዚህ ሁለት ሶስት ዓመታት ከውስን ቁጥር ተነስቶ ሊበዛ ቻለ ብለንም ልንጠይቅ ይገባል። ስለዚህ የሰላማዊ ፖለቲካን ማፈን ውጤቱ ለኛም ብቻ ሳይሆን ለመንግስትም ለአገርም አይበጅም። የመንግስት ካድሬዎች እኮ እንደፈለጉ አይንቀሳቀሱም አሁን እኔም የትውልድ ስፍራዬ አምቦ መሄድ አልቻልኩም፤ ሁለት ዓመታት አልፎኛል”ብለዋል። 

የሁለት ጉምቱ ፖለቲከኞች ስደት አንድምታ

ኦፌኮ ስላቀረበው ክስ እስካሁን የተሰማ የመንግስት ምላሸ የለም። ኦፌኮ በዚህ መግለጫ መንግስት ሰላምን ለማምጣት እየጣርኩ ነው ከሚል ንግግር ባሻገር በሰላማዊ መንገድ ከሚታገዱ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በሀቀኝነት እንዲመክርም ጠይቆ የአመራሮቹ እና አባላቱም እስራት እንዲቆም አሳስቧል።

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ