1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት የውይይት ጥሪ

ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2016

የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት ሁሉን አቀፍ ሀቀኛ የፖለቲካ ውይይት እና ብሔራዊ እርቅ እንዲደረግ ጠየቀ።16 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበው ህብረቱ አገሪቱ አሁን ለገባችበት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መፍትሄው በትጥቅና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን ኃይላት ማግባባት ላይ በማድረስ ነው ብሏል።

https://p.dw.com/p/4YqAD
The Ethiopian Political Parties Joint Council 09.06.2023
ምስል Solomon Muchie/DW

ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ የውይይት ጥሪ

የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት ሁሉን አቀፍ ሀቀኛ የፖለቲካ ውይይት እና ብሔራዊ እርቅ እንዲደረግ ጠየቀ። የፓርቲዎቹ ህብረት አገሪቱ አሁን ለገባችበት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መፍትሄው በትጥቅና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን ኃይት ማግባባት ላይ በማድረስ ነው ።16 የፖለቲካ ፓርቲዎች ገደማ አባል የሆኑበት የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት (ኮከስ) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተወሳሰበ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች ያለ ሲሆን፤ ዘላቂና እውነተኛ መፍትሄውም የሚመጣው ሁሉንም ባሳተፈ ፖለቲካዊ ውይይት መሆን ይገባዋል ሲል ጠይቋል፡፡በአሁኑ ጊዜ የብሔራዊ እርቅ እና አገራዊ መግባባት ፍላጎቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንም ያሳወቀው የፓርቲዎቹ ህብረት ሃቀኛ እና ተዓማኒ ብሔራዊ መግባባት መደረግ እንደሚገባው አደረኩ ባለው ግምገማ በመፍትሄነት ማስቀመጡንም አንስቷል፡፡የኢትዮጵያው ቀውስና የድርድር ፈተና
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ከኮከሱ አባላት አንደኛው ነው። የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ከፍተኛ አመራር አቶ ሙላቱ ገመቹ ከዚሁ ጋር አያይዘው ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት፤ ፓርቲያቸው በተለይም በኦሮሚያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አጥብቆ ይሻል ብለዋል፡፡ “ኦሮሚያ ሰፊ የሆነ የቆዳ ስፋት ያለውና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በህዝብም መስተጋብር በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችል ሁሉም ብሔር ብሔረሰብ የሚገኙበት ክልል ነው፡፡ በዚህ ክልል ውስጥ ሰላም ማስፈን ማለት በአጠቃላይ በ60 ከመቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እንደማስፈን ይቆጠራል፡፡ አሁን አገር የሚስተዳድረው መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር የሚያደርገውን ድርድርም በጉጉት የምንጠብቀው ነው፡፡ በዘላቂነት በኦሮሚያ እርቅ ሊያወርድ በሚችል መንገድ ከተከናወነም አገሪቷ በሰላም እንድትኖር የሚስችል መሰረት ሆናል የሚል ግምት ነው ያለን” ብለዋል፡፡
የሰላም መታጣት እና የፖለቲካው ቀውስ አዙሪት በኢትዮጵያአቶ ሙላቱ አክለውም የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት እና ጥያቄ ይህ ነው ብለዋል፡፡ “እራሱን በራሱ ማስተዳደር፤ በራሱ ክልል ላይ በራሱ የመወሰን ስልጣን፤ በራሱ መብት የመጠቀም እና በራሱ ቋንቋ እስከ ብሔራዊ መጠቀም እስካሁንም የታገለለት ኣላማ ነው፡፡ እነዚህን ነጻነቶች በአገሪቱ ውስጥ ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር የመጠቀም ፍላጎት ነው የህዝቡም ትግል፡፡ በዚህ ላይ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ከተካሄደና የራሱን መሪ ማስቀመጥ ከቻለ ሌላስ ምን ጥያቄ ይኖረዋል” ሲሉ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ባሉት ሃሳብ ላይ ሞግተዋልም፡፡

የተቃዋሚ ፓለቲካ ድርጅቶቹ ኮከስ ባቀረበው ምክረ ሃሳቡም መንግስትን የሚመራው ገዢው ፓርቲ ለሀቀኛ እና አካታች ውይይት እራሱን እንዲያዘጋጅ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች የተስፋፋው ግጭት ሰላማዊ እልባት እንዲያገኝ ስል ጥሪውን አቅርቧልም፡፡
ሰላማዊ ድርጅቶችን ገፍቶ ከታጣቂዎች ጋር ብቻ ለድርድር በር መክፈት ጥሩ መልእክት አያስተላልፍም፡፡ በመሆኑም ሀቀኛና ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ድርድር እና የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ይገባል” ሲል ህብር ፓርቲ አስታውቋል። ምስል Solomon Muchie/DW

ሌላው የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ኮከስ አባል ከሆነው ህብር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ፤ የፖለቲካ ህብረቱ ዋነኛ ጥሪ ሁሉን አካታች ውይይት እንዲደረግ ነው ብለዋል፡፡ “እንግዲህ እኛ በተደጋጋሚ ያቀረብነው ጥሪ ሁሉን አቀፍ፣ አካታች እና አሳታፊ ሀቀኛ ብሔራዊ መግባባት እና ድርድር መድረክ ተፈጥሮ የፖለቲካ ድርድር ተደርጎ በአገራችን ከ50 ዓመታት በላይ ስር የሰደደውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመቀየርና ለአገሪቱ የጋራ መፍትሄ ለማፈላለግ ሀቀኛ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ አገራዊ እርቅ እንዲፈጠር ነው። በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች በንቃት መሳተፍ አለባቸው ብለን እናምናለን፡፡”አቶ ግርማ አክለውም በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ውይይቶች እና ድርድሮች መንግስት ከታጠቁ አካላት ጋር ብቻ የሚያደርግ ውይይት እና ድርድር መሆን እንደማይገባው በአጽእኖት አንስተዋል፡

16 የፖለቲካ ፓርቲዎች ገደማ አባል የሆኑበት የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት (ኮከስ) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተወሳሰበ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች ያለ ሲሆን፤ ዘላቂና እውነተኛ መፍትሄውም የሚመጣው ሁሉንም ባሳተፈ ፖለቲካዊ ውይይት መሆን ይገባዋል ሲል ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት ሁሉን አቀፍ ሀቀኛ የፖለቲካ ውይይት እና ብሔራዊ እርቅ እንዲደረግ ጠየቀ። የፓርቲዎቹ ህብረት አገሪቱ አሁን ለገባችበት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መፍትሄው በትጥቅና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን ኃይት ማግባባት ላይ በማድረስ ነው ።ምስል Seyoum Getu/DW

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ“ችግር በሚከሰትበት ጊዜ በመጀመሪያ ችግሮችን በመካድ፤ ከዚያም ችግሮቹ አፍጠው ሲመጡ በተናጠል ከታጣቂዎች ጋር ከሚደረግ ውይይት በተጨማሪ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ጋር ውይይት መደረግ አለበት፡፡

ሰላማዊ ድርጅቶችን ገፍቶ ከታጣቂዎች ጋር ብቻ ለድርድር በር መክፈት ጥሩ መልእክት አያስተላልፍም፡፡ በመሆኑም ሀቀኛና ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ድርድር እና የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ይገባል” ነው ያሉት፡፡የተቃዋሚ ፓለቲካ ድርጅቶቹ ኮከስ ባቀረበው ምክረ ሃሳቡም መንግስትን የሚመራው ገዢው ፓርቲ ለሀቀኛ እና አካታች ውይይት እራሱን እንዲያዘጋጅ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች የተስፋፋው ግጭት ሰላማዊ እልባት እንዲያገኝ ስል ጥሪውን አቅርቧልም፡፡

ሥዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ