1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኅብረተ ሰብየመካከለኛው ምሥራቅ

እስራኤል በራፋሕ ላይ የከፈተችው ጦርነት

ሐሙስ፣ ግንቦት 8 2016

ቀደም ሲል በጦርነቱ ምክንያት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፍልስጤሞች በእስራኤል መንግስት አስገዳጅነት ጭምር ወደ ደቡባዊው ክፍል በተለይም ወደ ራፋ ከተማ እንዲሰደዱ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ፤ በራፋሕ በተከፍተው ጦርነት ምክንያት ካንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ ተፈናቃዮች ዳግም እንዲፈናቀሉ ተገድደዋል።

https://p.dw.com/p/4fwpe
Gaza Die israelische Armee veranlasst die Palästinenser nach Deir al-Balah auszuwandern
ምስል Ashraf Amra/Anadolu/picture alliance

በጋዛ ጉዳይ የአውሮጳ ኅብረት ውግዘትና የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ጥሪ

ደቡብ አፍሪቃ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፍርድ ቤት በመቅረብ እሥራኤል ላይ ያቀረበችውን የክስ ሒደት አጠናክራለች ። ደቡብ አፍሪቃ ጋዛ ውስጥ «የዘር ማጥፋት» ያለችውን ድርጊት እሥራኤል በአስቸኳይ እንድታቆም ስትልም በራፋሕ ላይ የተጠናከረው ጥቃት እንዲቋረጥም ፍርድ ቤቱን ጠይቃለች ። ጦርነቱን ሸሽተው ከወደመ መንደራቸው ወደ ራፋሕ ለመሰደድ የተገደዱ በበርካታ ሺህ የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን በእሥራኤል የሰሞኑ የተጠናከረ የራፋሕ ድብደባ ለዳግም ስደት መዳረጋቸው ተዘግቧል ። 

በእስራኤልና ምራባውያን መንግስታት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሐማስ መስከረም 26 በሰላማዊ የእስራኤል ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ የክፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ እስካሁንምበአስከፊ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።  እስካሁን በጦርነቱ ከ35 ሺ በላይ ብዙዎቹ እናቶችና ህጻናት የሆኑ ፍልስጤሞች እንደተገደሉና 80 ከመቶ የሚሆነው የጋዛ ሰርጥ መሰረተ ልማትም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እንደወደመ የመንግስታቱ ድርጅት መረጃዎች ጭምር ያስረዳሉ።

ቀደም ሲል በጦርነቱ ምክንያት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፍልስጤሞች በእስራኤል መንግስት አስገዳጅነት ጭምር ወደ ደቡባዊው ክፍል በተለይም ወደ ራፋ ከተማ እንዲሰደዱ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ፤ በራፋሕ በተከፍተው ጦርነት ምክንያት ካንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ ተፈናቃዮች ዳግም እንዲፈናቀሉ ታዘዋል። እስራኤል በራፋ ጦርነት እንዳትከፍት በበርካታ መንግስታትና በፕሬዝድንት ባይደን ሳይቀር ተጠይቃ ነበር። ወደ ራፋ ጦር የምታዘምት ከሆነም አሜሪካ የምትልከውን የጦር መሳሪያ እንደምታዘገይ ዐስታውቃ ነበር፤ ምንም እንኳ ባለፈው ማክሰኞ የጦር መስሪያ የተላከ መሆኑ ቢገለጽም።

የአውሮጳ ኅብረት ውግዘትና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጥሪ

ያውሮጳ ኅብረትና አባል መንግስታቱ ግን እስራኤል በተለይ በራፋሕ ላይ የከፍተችውን ጦርነት አጥብቀው ነው ያወገዙት።  ህብረቱ ክትናንት ወዲያ ባወጣው መግለጫ ኢስራኤል በራፋ የከፈተችውን ወታደራዊ ዘመቻ ባስቸኳይ እንድታቆምና የዘጋችውን የራፋ የርዳታ መግቢያ በር እንድትከፍት ጠይቋል። ህዝቡን ለባሰ ችግርና ርሀብ ኪሚዳርጉና፤ ግጭቱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች እንድትቆጠብም አሳስቧል። የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ቦርየል ከዚህም አልፈው በፍልስጤም ህዝብ ላይ እየተፈመ ያለው ጥቃት ከመጠን ያለፈ ነው የሚሉ መንግስታት ተጨባጭ እርምጃ በመውሰድ የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ፕሬዝደንት ባይደንን በመጥቀስ ጭምር አሳስበዋል። " ፕሬዝድንት ባይደን እስራኤል እየወሰደችው ያለው እርምጃ ከመጠን ያለፈ ነው ያላሉ ፣ ብዙ ህዝብ እየተገደለ መሆኑን ካመኑ፤ መፍትሄው የሚልኩትን የጦር መሳያ ቢያንስ መቀነስ ነው”  በማለት ቅሬታቸውን ጭምር አሰምተዋል። ሚስተር ቦርየል የጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ መንግስት ፍልስጦሞች ከራፋ እንዲለቁ ላቀረበው ጥያቄ ውዴት ይሂዱ? በማለት መልሰው ሲጠይቁም ተሰምተዋል።

ጋዛ ሰርጥ፤ ምሥራቅ ራፋሕ
ጋዛ ሰርጥ፤ ምሥራቅ ራፋሕምስል -/AFP

ከራፋሕ የተፈናቀለው ሕዝብና የሰላም ድርድሩ ያለበት ሁኔታ

እንዲህም ሆኖ ግን ጦርነቱ እንደቀጠለና ካለፈው ሳምንት ወዲህ ብቻ ከራፋ ከ600፣ ሺ በላይ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ነው እየተገለጸ ያለው። በቃታርና ግብጽ አደራዳሪንት፤ በሀማስና እስራኤል መካከል  ሲካሄድ የነበረው የስላም ድርድርም በአሁኑ ወቅት እስራኤል በራፋ በክፍተችው ጦርነት ምክኒያት ወደፊት ሊራመድ አለመቻሉን ዋና አደራዳሪ የነበሩ የቃታር ጠቅላይ ሚኒስተር ሼህ ሞሃመድ ቢን አብዱርህማን አስታውቀዋል፡ "በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጥሩ መግባባት እየታየ ነበር; ባሁኑ ወቅት ግን ነገሮች በተፈለገው አቅጣጫ እየሄዱ ባለመሆኑ ድርድሩ ባለበት ቁሟል ማለት ይቻላላል። እውነት ነው በራፋ እየሆነ ያለው እንቅስቅሴያችንን ገቶታል”  በማለት ለሰላም  ድርድሩ መቋረጥ ኢስራኤልን ተጠያቂ ድረገዋል።

የግብጽ ደቡብ አፍሪቃን መቀላቀልና ምክንያቶቹ

ግብጽ በበኩሏ ከእንግዲህ ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለማቀፉ ፍርድቤት እስራኤልን ከከሰሰቸው ደቡብ አፍሪቃ ጋር እንደምትተባበርና ከሷ ጎን እንድምትቆም አስታውቃለች። ደቡብ አፍርካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፍት ወንጀል ክስ የመረመረው ዓለምዓቀፉ ፍርድቤት፤ እስራኤል አስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎችና እርምጃዎችን እንድትወስድ ቢወስንም፤ እስራኤል ግን ውሳኔውን እያከበረች አይደለም በማለት ደቡብ አፍርካ አሁንም በመከራከር ላይ ነች።

 ዘ ሄግ የሚገኘው ዓለማቀፉ ፍርድ ቤት
ዘ ሄግ የሚገኘው ዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ምስል Peter Dejong/AP/dpa/picture alliance

ግብጽ ካደራዳሪነት ወጥታ በፍጥነት ደብቡ አፍርካን በመቀላቀል እስራኤልን ለመሞገት የወሰነችባቸውን ምክኒያቶች  ከቃታር ዩንቨርስቲ ሚስተር ማሂጃብ ዝዌይሪ ያስረዳሉ፤ "አንደኛው ግብጾች፤ እስራኤል  በራፋ ላይ በወሰደችው እርምጃ ተበሳጭተዋል። ዘመቻው ከመጀመሩ ጥቂት ሰአታት በፊት ነው ያሳወቋቸው፡፤ ሁለተኛው በግብጾች የተዘጋጀውንና ከእስራኤል መንግስት ጋር ብዙ ውይይት ተደርጎበት የቀረበውን የሰላም ሀሳብ ሃማስ ሲቀበለው እስራኤል መቃወሟ ግብጾችን ሳያሳዝናቸው አልቀረም በማለት ይህም ሌላው ምክኒያት ሊሆን እንደሚችል ገለጸዋል።በጦርነቱም መሀል ቢሆን

የፍልስጤም አገርነት ዕውቅና እያገኘ መሆኑ

እስራኤል ያለማቀፉ ማኅብረሰብና ወዳጆቿ ጭምር የሚያቀርቡትን የሰላም ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በከፍተችው ዘመቻ  እየደረሰባት ካለው ውግዘት ባለፈ፤  ባለፈው ሳምንት የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤምን የድርጅቱ አባል ለመሆን የሚያስችሉ መስፈርቶችን የምታሟ ናት በማለት በክፍተኛ የድምጽ ብልጫ የወሰነ መሆኑ ተገልጿል። በአውሮጳም ቢያንስ  የተወሰኑ የአውሮጳ ኅብረት አባል አገራት በዚህ ወር መጨረሻ ለፍልስጤም አገርነት ዕውቅና ይሰጣሉ እየተባለ ነው።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ