1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤል ለጋዛ ዕርዳታ እንዳይደርስ መከልከሏን እንድታቆም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አዘዘ

ዓርብ፣ መጋቢት 20 2016

ደቡብ አፍርካ ውሳኔውን በጣም በማለት አፈጻጸሙን እንደምትከታተል ስታስታውቅ፤ የፍልስጤም አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ቢሮ ደግሞ እርምጃው በአለማቀፍ ደረጃ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች የሚያመላክት ነው በማለት ደቡብ አፍርካን አመስግኗል።

https://p.dw.com/p/4eGC6
ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያደርሱ እርምጃዎች እንዳስትወስድ ባለፈዉ ጥር ወስኗል።
ዘ-ሔግ ኔዘርላንድ የሚያስችለዉ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት ደቡባ አፍሪቃ በእስራኤል ላይ ያቀረበችዉን ክስ በሚያስችልበት ወቅት ምስል Piroschka van de Wouw/REUTERS

እስራኤል ለጋዛ ዕርዳታ እንዳይደርስ መከልከሏን እንድታቆም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አዘዘ

ዘሄግ የሚገኘው ዓለማቀፍ ፍርድ ቤት ትናንት ሀሙስ ባስቻለው ችሎት፤  እስራኤል ወደ ጋዛ የሰባዊ እርዳታ በፍጥነትና በበቂ ሁኔታ እንዲገባ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንድትወስድ የሚጠይቅ ተእዛዝ አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ጥር ወር ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ አቅርባው በነበረው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ  በሰጠው ብይን፤ እስራኤል ማናቸውንም የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ከሚያስችሉ ወታደራዊ እርምጃዎች እንድትቆጠብ፣ ህዝብን በገፍ ሊጨርሱ ከሚችሉ እርዳታን እንዳይደርስ የማድረግ እርምጃዎችን እንዳትወስድ መጠየቁና ትዕዛም ማስተላለፉ የሚታወስ ነው።

ድጋሜ ትዕዛዝ ያስፈለገበት ምክኒያት

ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ወዲህ ግን የጋዛ ሁኔታ ከመሻሽል ይልቅ እንደባሰበትና በጦርነት ከሚሞቱት አልፎ  መላ ህዝቡ ለክፍተኛ እረሀብ የተጋለጠ መሆኑን  የመንግስትቱ ድርጅት  በአቅርቡ ባወጣው ርፖርት ይፋ አድርጓል። ደቡብ አፍሪካም ይህንን የተባባሰውን የጋዛን ሁኒታና የገባውን እረሀብ በመጥቀስ ፍርድ ቤቱን ለውሳኔው ግባራዊነት በእስራኤል ላይ በድጋሜ ትዛዝ እንዲያስተላለፍለት በጠየቀው መሰረት፤ ይህ ትዛዝ እንደተላለፈ ታውቁል። የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ባለፈው ጥር ወር ከተላለፈው ውሳኔ በተጨማሪ፤ እስራኤል  የእርዳታ መተላለፊያዎችን በምድር ጭምር  ክፍት እንድታደርግ የሚጠይቅና  ባንድ ወር ግዜ ውስጥም የአፈጻጸሙ ሪፖርት እንዲቀርብለት የሚያዝ ነው።

በውሳኔው ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ደቡብ አፍርካ ውሳኔውን በጣም  በማለት አፈጻጸሙን እንደምትከታተል ስታስታውቅ፤ የፍልስጤም አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ቢሮ ደግሞ እርምጃው በአለማቀፍ  ደረጃ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች የሚያመላክት ነው በማለት ደቡብ አፍርካን አመስግኗል። በአሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረትና እስራኤል በሸባሪነት የተፈረረጀው ሀማስ በበኩሉ ውሳኔው በአለማቀፍ ማህብረሰቡ ጭምር ተግባራዊ እንዲሆን መጠየቁ ተዘግቧል። 

ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያደርሱ እርምጃዎችን እንዳትወስድ በወሰነበት ችሎት የተገኙት የደቡብ አፍሪቃ ልዑካን
ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያደርሱ እርምጃዎችን እንዳትወስድ በወሰነበት ችሎት የተገኙት የደቡብ አፍሪቃ ልዑካን ምስል Piroschka van de Wouw/REUTERS

 እስራኤል ግን በሰላማዊ  ሰዎች ላይ ጥቃትእንዳይደርስና እርዳታም እንዲገባ ለማድረግ የበኩሏን  እያደረገች መሆኑን በመግለጽ፤  ደቡብ አፍሪካ፤ የአለማቀፉን ፍርድ ቤት በማሳሳት ጭምር የእስራኤልን እራሷን ከጥቃት የመከላከል መብት በመጋፋት ከሳለች ። የፍልስጤም ብሄራዊ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ሚስተር ሙስተፋ ባሩቲም  ውሳኔው ጥሩ እርምጃ መሆኑን ነው የገለጹት። “ ጥሩ እርምጃ ነው ግን ውሳኔው ተግባራዊ ለመሆን  የተኩስ አቁም ስምምነት መኖርንና የጦርነቱንም መቆም ይጠይቃል። ለዚህም አለማቀፉ ፍርድቤት ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቅ ውሣኔም  ማሳለፍ ይኖርበታል” በማለት እስራኤል ማዕቀብ ክልተጣለባት በስተቀር  ከዚያ መለስ ባሉ ሌሎች  ውሳኔዎች የምገትደድ መሆኑን እንደሚጠራጠሩ ግልጽ አድርገዋል።

የውሳኔው ተግባራዊነት አጠራጣሪነት

የፍርድቤቱ ውሳኔና ትዛዞቹ ብቻቸውን ለውጥማምጣታቸውን የሚጠራጠሩት የፍስልጤም ባለስልጣኖች ብቻ አይደሉም። በዶሃ ዩንቨርሲት የመካከለኛው ምስራቅ ፕሮፊሰር  የሆኑት ዶክተር ማርክ ኦውን ጆንስም ካለፈው የፍርድ ቤት ውሳኔ ወዲህ በጋዛ  የእርዳታ አቅርቦቱ እንደውም የቀነሰ መሆኑን በመጥቀስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ብቻውን ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችል ነው የሚናገሩት፤ “  ያለማቀፉ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ ማለት እስራኤል ተግባራዊ ታደርጋለች ማለት አይደለም። ለጋዛ ህዝብ በቂ እርዳታ በአስተማማኝ ሁኔታ ሊደርስ የሚችለው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ሲደረስ ብቻ” መሆኑን ገልጸዋል።

በቤልጅየም ጌንት ዩንቨርስቲ የሰባዊ መብት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ብሪጂት ሄርማንስም የዓለዓማቀፉ ፍርድቤት ውሳኔ  አስገድጅ ነው ቢባልም አስፈጻሚ ግን እንደሌለው ነው የሚናገሩት፤ “ በዕርግጥ የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ውሳኒዎችና ትዛዞች አስገዳጆች ናቸው። ግን አስፈጻሚ አካል የሌላቸው በመሆኑ ተግባራዊ ሳይሆኑ ይቀራሉ” በማለት በፍርድ ቤቱ አሰራርና አፈጻሰም ያሉትን ችግሮች ጠቅሰዋል።

ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያደርሱ እርምጃዎችን እንዳትወስድ በወሰነበት ችሎት የተገኙት የእስራኤል  ልዑካን
ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያደርሱ እርምጃዎችን እንዳትወስድ በወሰነበት ችሎት የተገኙት የእስራኤል ልዑካን ምስል Piroschka van de Wouw/REUTERS

 በአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሀማስ ባለፈው መስከረም 26 በሰላማዊ የእስራኤል ዜጎች ላይ የፈጸመውን ግድያና ጠለፋ ተክትሎ፤ እስራኤል ባለፉት አምስት ወራት ባጋዛ ላይ በከፈተችው ጦርነት፤ እስካሁን ከ32 ሺበላይ ስለማዊ ሰዎች እንደሞቱና ከሰባ ሺ በላይ እንደቆሰሉ ይፋ ሁኗል። ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ወደ አካባቢው እርዳታ እንዳይገባ በመከልከሉ  ወይም በበቂ ሁኔታ ባለመድረሱ ካአጠቃላዩ የጋዝ 2.2 ሚሊዮን ህዝብ 70 ክመቶ የሚሆኑት ለክፋ እረሀብ ተዳርገው በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸው በመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርቶች ጭምር ተተገልጿል።

ገበይው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ