1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ዓርብ፣ ነሐሴ 28 2013

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ አይነተኛ አሻራን ካሳረፉ አንጋፋው የሙዚቃ ሰዎች አንዱ  ዓለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

https://p.dw.com/p/3ztRW
Der äthiopische Sänger und Songwriter Alemayehu Eshete
ምስል Pablo Ruiz Holst

«ቀብሩ እሑድ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ይሆናል»

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ አይነተኛ አሻራን ካሳረፉ አንጋፋው የሙዚቃ ሰዎች አንዱ  ዓለማየሁ እሸቴ ማረፉ ተሰምቷል። የድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ሕወይት ያለፈው ትናንት አመሻሽ ከልብ ህመም ጋር ተያይዞ ሆስፒታል በገባ በሰዓታት ውስጥ መሆኑን ዶይቼ ቬለ ከቤተሰቡ ተረድቷል። የአንጋፋው ሙዚቀኛ ስርዓተ ቀብርም የፊታችን እሑድ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ,ም በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በብሔራዊ የአሸኛነት ስርዓት እንደሚፈጸም በጊዜያዊነት የተያዘው መርሃ-ግብር ያመለክታል።

ስዩም ጌቴ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ