1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የአፍሪቃ ወቅታዊ ሁኔታ

ቅዳሜ፣ ጥር 28 2014

35 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት ሥጋት አዲስ አበባ ላይ ለሁለት ዓመታት ሳይካሄድ ከቆየ በኋላ ዛሬ በሕብረቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ላይ ተደርጓል። ለአህጉሩ ሰላምና ደህንነት በውስን አቅም እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ዕቅዱን በቁርጠኝነት መተግበር አለመቻሉ ወደኋላ የሚጎትት መሆኑን ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/46a4l
Äthiopien Addis Ababa | Afircan Union Gipfel
ምስል Solomon Muchie/DW

በምዕራብ አፍሪቃ እየታየ ያለው የመፈንቅ ለመንግስት አፍሪቃን ዳግም ወደ ኋላ እየጎተታት ነው

35 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት ሥጋት አዲስ አበባ ላይ ለሁለት ዓመታት ሳይካሄድ ከቆየ በኋላ ዛሬ በሕብረቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ላይ ተደርጓል።
በሕብረቱ የመክፈቻ ሥና ሥርዓት ላይ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ተሰናባቹ እና አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመናብርት ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዚህም የአህጉሩን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ ምርታማነትን በማሳደግ የዘላቂ ልማት ግብን ማሳካት፣ በአህጉሩ ሕገ ወጥ የመንግሥት ለውጥን ማስወገድ፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነትን ማሳደግ፣ የኢኮኖሚ አቅምን ማጠናከር እና የአየር ንብረት ጥበቃ ላይ ጠንክሮ መሥራት ይገባል የሚሉ ሀሳቦች ተንፀባርቀዋል።
ሕብረተ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ተመጣጣኝ ቋሚ እና ተለዋጭ ውክልና እንዲያገኝም ተጠይቋል።
አፍሪካ ለአህጉሩ ሰላምና ደህንነት በውስን አቅም እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ዕቅዱን በቁርጠኝነት መተግበር አለመቻሉ በምዕራብ የአህጉሩ ክፍል የሚስተዋለው አዝማሚያ ወደኋላ የሚጎትት መሆኑን አንድ የሰላምና ደህንነት ተንታኝ ተናግረዋል።

Äthiopien Addis Ababa | Afircan Union Gipfel
ምስል Solomon Muchie/DW
Äthiopien Addis Ababa | Afircan Union Gipfel
ምስል Solomon Muchie/DW

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ