1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ጡረተኞች አቤቱታቸው መልስ ማግኘት ጀመረ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 28 2016

በተደጋጋሚ የጡረታ አበላቸው እንዲከፈላቸው ሲጠይቁ ለነበሩ በትግራይ የሚገኙ ጡረተኞች የፌደራሉ መንግስት 1.6 ቢልዮን ብር መድቦ ክፍያቸውን መስጠት መጀመሩ ተገለፀ። ጡረተኞቹ የ17 ወር የጡረታ አበላቸው እንዲከፈል በተደጋጋሚ ሲጠይቁ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ነበር።

https://p.dw.com/p/4eV6B
Äthiopien | Demonstration in Tigray
ምስል Million Haile sillasie

በትግራይ ክልል የሚገኙ ጡረተኞች አቤቱታቸው መልስ ማግኘት ጀመረ

በተደጋጋሚ የጡረታ አበላቸው እንዲከፈላቸው ሲጠይቁ ለነበሩ በትግራይ የሚገኙ ጡረተኞች የፌደራሉ መንግስት 1.6 ቢልዮን ብር መድቦ ክፍያቸውን መስጠት መጀመሩ ተገለፀ። ጡረተኞቹ የ17 ወር የጡረታ አበላቸው እንዲከፈል በተደጋጋሚ ሲጠይቁ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ነበር።

ትግራይ ክልል የጡረተኞች የተቃውሞ ሰልፍ

ሊከፈላቸው የሚገባ የ17 ወራት የጡረታ አበል እንዳላገኙ የሚገልፁ በትግራይ ያሉ ጡረተኞች፥ ክፍያቸውን እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ በተደጋጋሚ ጥያቄአቸው ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ለነዚህ በትግራይ የሚገኙ ጡረተኞች መፍትሔ መስጠቱ የሚገልፀው የመንግስት ሰራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና አስተዳደር መንግስት 1 ነጥብ 6 ቢልዮን ብር በመመደብ የጡረተኞቹ የጦርነቱ ወቅት የ17 ወራት ክፍያቸው መስጠት መጀመሩ ይገልፃል።

Äthiopien | Demonstration in Tigray
ምስል Million Haile sillasie

በመንግስት ሰራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ሪጅን ፅሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ተወለደ ለማ ተቋማቸው ከመንግስት ሰራተኞች መዋጫ ሳይሰበስብ የጡረታ አበል መክፈል ተቸግሮ መቆየቱ በማንሳት የፌደራሉ መንግስት ችግሩ ለመፍታት 1 ነጥብ 6 ቢልዮን ብር መልቀቁ ተከትሎ የጡረታ ክፍያው መሰጠት መጀመሩ ለዶቼቬለ ገልፀዋል።

ትግራይ ክልል የሚገኙ ጡረተኞች አቤቱታ

እንደ ሐላፊው ገለፃ በትግራይ ካሉ ጡረተኞች መካከል ከ65 ሺህ በላይ የሚሆኑ ክፍያው በባንክ በኩል ይደርሳቸዋል።

በመንግስት የተከለከለ የጡረታ አበላችን ይከፈለን በማለት በተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርብ፣ ሰልፍ ያደርግ የነበረው የጡረተኞች ተቋሙ የመቐለ ጡረተኞች ማሕበር በበኩሉ ውዝፍ የጡረታ ክፍያው ለሁሉም ጡረተኛ ስለመድረሱ የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራ ገልጿል። ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኃላ መፍትሔ መገኘቱ ጡረተኛው አስደስቷል የሚሉት የመቐለ ጡረተኞች ማሕበር ሊቀመንበሩ ዶክተር ገብረሚካኤል ንጉሰ፥ በመሰረቱ ግን መደረግ ያልነበረበት ተግባር ብለውታል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ