1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትንሳኤ በዓል አከባበር በኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት 

እሑድ፣ ሚያዝያ 16 2014

በአዲስ አበባ በሚገኙት ሰዓሊተ ምህረት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ካህናት ከቅዳሜ ምሽት ሥርዓተ ቅዳሴ ሲከወን፣ ጸሎት እና ምሥጋና ሲደረግ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ተገኝቶ ነበር።

https://p.dw.com/p/4AMVz
Äthiopien Addis Abeba | Messe Katholische Kirche St. Joseph
ምስል Solomon Muchie/DW

የትንሳኤ በዓል አከባበር በኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት 

በክርስትና እምነት አማንያን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሣኤ በዓል ዛሬ እየተከበረ ነው።

ትናንት በትንሣኤው ዋዜማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስትያናት በተለይም የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በተዋበ መንፈሳዊ ክዋኔ ከምሽቱ ሦስት እስከ ሌሊቱ አሥር ሰዓት ተፈፀማል።

Äthiopien Addis Abeba | Sealite Mihret Kidist Mariam Kirche
አዲስ አበባ ጉድር ሾላ የሚገኘው ሰዓሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ጉድር ሾላ በሚገኘው ሰዓሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን እና ጎሮ አካባቢ በሚገኘው በአዲስ አበባ አገረ ስብከት የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የዋዜማው ምሽት እና ሌሊት ድምቀት በተሞላው መንፈሳዊ ሥርዓት ዋዜማው ትከብሯል።

ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ