1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሙዚቃአፍሪቃ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ሳክስፎን ተጫዋች ሀና

ሰኞ፣ ነሐሴ 24 2013

የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊዲያ መለስን ጨምሮ 60 የሚሆኑ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ድሬደዋ በሚገኘው የትምህርት ቢሮ የተማሪዎች ማርሽ ባንድ ውስጥ የሙዚቃ መሣሪያዎች መጫወት ይሰለጥናሉ።

https://p.dw.com/p/3zfi1

ከእነዚህ አንዷ የሆነችው  ሀና የኔው በተማሪዎች ማርሽ ባንዱ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የሳክስፎን ሙዚቃ መሣርያ ትጫወታለች። የ 12ኛ ክፍል ተማሪዋ ሌሎች መሣሪያዎችንም መጫወት ትችላለች። የማርሽ ባንዱ መስራች እንደሚሉት «ሀና ከፍተኛ ችሎታ ያላት ልጅ ናት»። ሀና ይህን ችሎታዋን ወደፊትም ከትምህርቷ ጎን ለጎን ማስኬድ ትፈልጋለች። ሌሎች አዳጊ ሴቶችን የምትመክረውም ይህንን ነው።

ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ