1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 19 2015

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ለአንባቢዎች ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ዘገባው በጎርጎሪዮሱ 2022 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ «እጅግ ገዳዩ ግጭት የነበረው በዩክሬን ሳይሆን በኢትዮጵያ ነበር» ብሏል ። ዓመታዊ ዘገባው በደሉ የተፈጸመውም «ከዓለም የትኩረት አቅጣጫ ውጪ ነው» ነው ሲል አስነብቧል

https://p.dw.com/p/4PNp4
Amnesty international Logo
ምስል picture-alliance/dpa/S.Kahnert

«እጅግ ገዳዩ ግጭት ዩክሬን ሳይሆን ኢትዮጵያ ነበር»

ዛሬ ለአንባቢዎች ይፋ የሆነው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባ በጎርጎሪዮሱ 2022 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ «እጅግ ገዳዩ ግጭት ዩክሬን ሳይሆን ኢትዮጵያ ነበር» ብሏል ። ዓመታዊ ዘገባው በደሉ የተፈጸመውም «ከዓለም የትኩረት አቅጣጫ ውጪ ነው» ነው ሲል አስነብቧል ። «ኢትዮጵያን ጨምሮ በሚያንማር እና በየመን በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተገደሉበት ግጭቶች ዓለም አቀፍ ተቋማት በቂ ምላሽ አልሰጡም» ሲልም ወቅሷል ። ያለፈው የጎርጎሪዮሱ ዓመት የሴቶች መብቶችም ያሽቆለቆለበት እንደሆነ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ጠቅሷል ። ብዙ ግድያዎች እና ዝርፊያዎ፤ ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ በደሎች እና ሕገ ወጥ ወንጀሎች በበርካታ የዓለማችን አካባቢዎች ተካሂዷልም ብሏል ። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር